የምድር ገሀነም
በፋኖ ሀይልና በመንግስት ወታደሮች መጠነ ሰፊ ጦርነት እየተደረገ ስለመሆኑ ይኸው ድፍን ሁለት ዓመት ሞላው። በዚህ የ ትጥቅ ትግል የ ግፍ ፅዋ ቀማሽ ንፁሀን ማህበረሰቡ መሆኑ የ አደባባይ ሀቅ ነው። ለዚህ ዋና ምክንያቱ የመንግስት ወታደሮች በ ደፈጣ ውጊያ ከ ፋኖ የሚሰነዘርባቸውን መቋቋም ሲያቅታቸው በየ ቤቱ እየበረበሩ ወጣት ማህበረሰቡን በ አሰቃቂ ሁኔታ ይረሽናሉ። በኔ ቤተሰብ የደረሰውን ለ አብነት ማንሳት ይቻላል። የ እኔ አጎት ሰላማዊ ሰው ሆኖ እያለ ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት አካባቢ ቤቱን ዘግቶ በተቀመጠበት የመንግስት ሀይል ድንገት አሰሳ በማድረግ ከቤት አውተው መንገድ ላይ በ አሰቃቂ ሁኔታ በ ጥይት ደብድበው ገድለውት ሄደዋል። ይህ ጠባሳ ለ ቤተሰብ ዘመድ አዝማዱ እና የ አካባቢው ማህበረሰብ ከ አዕምሮ በ ቀላሉ የሚወጣ አይደለም። መከላከያ ዩኒፎርም የለበሱ ታጣቂወችን ያዩ ህፃናት ጩኸት እያሰሙ ሲሮጡ ማየት የተለመደም ሁኗል ለዚህም መንስዔው የሚገደሉ ሰዎችን በ አይናቸው ማየታቸው ነው።