የምድር ገሀነም
በፋኖ ሀይልና በመንግስት ወታደሮች መጠነ ሰፊ ጦርነት እየተደረገ ስለመሆኑ ይኸው ድፍን ሁለት ዓመት ሞላው።
በዚህ የ ትጥቅ ትግል የ ግፍ ፅዋ ቀማሽ ንፁሀን ማህበረሰቡ መሆኑ የ አደባባይ ሀቅ ነው።ለዚህ ዋና ምክንያቱ የመንግስት ወታደሮች በ ደፈጣ ውጊያ ከ ፋኖ የሚሰነዘርባቸውን መቋቋም ሲያቅታቸው በየ ቤቱ እየበረበሩ ወጣት ማህበረሰቡን በ አሰቃቂ ሁኔታ ይረሽናሉ።
በኔ ቤተሰብ የደረሰውን ለ አብነት ማንሳት ይቻላል።
የ እኔ አጎት ሰላማዊ ሰው ሆኖ እያለ ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት አካባቢ ቤቱን ዘግቶ በተቀመጠበት የመንግስት ሀይል ድንገት አሰሳ በማድረግ ከቤት አውተው መንገድ ላይ በ አሰቃቂ ሁኔታ በ ጥይት ደብድበው ገድለውት ሄደዋል።
ይህ ጠባሳ ለ ቤተሰብ ዘመድ አዝማዱ እና የ አካባቢው ማህበረሰብ ከ አዕምሮ በ ቀላሉ የሚወጣ አይደለም።
መከላከያ ዩኒፎርም የለበሱ ታጣቂወችን ያዩ ህፃናት ጩኸት እያሰሙ ሲሮጡ ማየት የተለመደም ሁኗል ለዚህም መንስዔው የሚገደሉ ሰዎችን በ አይናቸው ማየታቸው ነው።
Comments
Post a Comment