አማራን ማገት አዲሱ የገቢ ምንጭ

 ዛሬ ብዙ ሰው ወደ አዲስ አበባ ሲሄድ ያው የተለመደው ኦሮምያ ውስጥ በኦሮሞ ታጣቂዎች እንደታገቱ፣ የአንደኛው አውቶብስ ሾፌሩ ሊያመልጥ ሲል በጥይት እንደተገደለ ሰማሁ። 

ባለፈው ወደ አዲስ አበባ በእውቶብስ ለእንግሊዝኛ ፈተና ስሄድ እኛ ከተሳፈርንበት አውቶብስ በሁዋላ የነበሩትን ሁለት አውቶብሶች አባይ ማዶ (ኦሮምያ ውስጥ) ከጎሃ ፂዮን አካባቢ ሲደርሱ በኦሮሞ ታጣቂዎች ታገቱ። እኛ በእድል አመለጥን።

ባሶችን አስቁመው አማራ የሆነውን ሰው እየለዩ ወደጫካ እየመሩ እንደወሰዱና ከዚያ ለማስለቅቂያ በሚሊዮን ካሳ እየጠየቁ፣ በጣም ጥቂቶቹ መክፈል የቻሉት ሲለቀቁ አብዛኛዎቹ ያልቻሉት ግን ምን እንደሆኑ አይታወቅም። አጋቾቹ የኦነግ ወታደሮች ናቸው ይባላል፣ ግን ደግሞ በአካባቢው ያሉ  የመንግስት ወታደሮች ምንም እንዳልተፈጠረ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አያደርጉም፣ እኛ ስናልፍ የተገነዘብነው ይሄንን ነው። የኦሮምያ ፖሊስ ሰዎች ግን ይሄን ሳይሰሙ ቀርተው ነው ማለት ይከብደኛል፣ እጃቸው ከሌለበት አንድ አሸባሪ ቡድን በጠራራ ከጎሃ ፂዮን ሁለት አውቶብስ ሲያግት ምን እየሰሩ ነው?

በአብይ ዘመን አማራ ሰፈሩ መሃል በመከላከያ፣ ኦሮምያ ውስጥ በኦነግ በየሄደበት እንደውሻ ተቀጥቅጦ ሊገደል ተፈርዶበታል። አማራን ማገት የሀብት ምንጭ ሁንዋል። መንግስት ለአማራ ግድ የለውም። የት እንሂድ?

Comments

Popular posts from this blog

አማራ ላይ ግልፅ የዘር ማጥፋት

History of Debre Markos City