አማራ የደም ምድር

 ባጭር ጊዜ ምድራችን ደም በደም ሆነ፣ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በደብረማርቆስና አካባቢ የሆነውንና የተደረገውን ነገር ሳስብ እንቅልፍ መተኛት አልቻልሁም።  በስላም ወጥቶ መግባት ናፈቀን፣ በየቀኑ የጥይትና የሞት ድምዕ ሰለቸን፣

ልጅነት ናፈቀን፣ ያለፍርሃት ኳስ መጫወትም እንዲህ ይርቃል? የሰላም አየር ከምድራችን ጠፍቷል፣ የአማራ ነፍስ ረክሷል።

መከላከያ ህዝብ ላይ ተኩሶ የሚገድልበት ዘመን ላይ ደረስን፣ ምን አይነት ዘመን ነው ግን? ለመነኩሴና ለህሳናት የማይራራ መከላከያ በጣም ያሳዝናል።



ግን አማራ ምን አጥፍቶ ነው፣ ጎጃም ምን በደለ? አርሶ ባበላ? በጣም ያሳዝናል!! ገዳም ውስጥ ያሉ ሰርተው የሚበሉ እነዚህ ሁለት ድሃ ልጆችስ ምን አጥፍተው ነው? ገዳም ጠበል ለመጠመቅ የሄዱ እናቶችና  ጡት የሚጠቡ ትናንሽ ልጆችስ ምን ቢበድሉ ነው በጥይት የሚደበደቡት?




Comments

Popular posts from this blog

አማራ ላይ ግልፅ የዘር ማጥፋት

History of Debre Markos City