አማራ ላይ ግልፅ የዘር ማጥፋት

 ክጥቅምት ጀምሮ መንግስት ኢንተርኔቱን ጥርቅም አድርጎ ሲገድለን ነው የከረመ።  አሁን ራሱ ኢንተርኔቱን ሊዘጋው ይችላል።

በደብረ ማርቆስ አካባቢ እየተሰራ ያለው ግፍ፣ የመንግስት ወታደሮች ጭካኔ፣ ጉዋደኞችን ጨምሮ ያለቀው ሰላማዊ ሰው፣ በቃ በምን ቃላት ይነገራል። ጠዋት ከአልጋየ ስነሳ ተረኛ ተረሻኝ ላለመሆኔ ምንም ዋስትና የለኝም። ህግ የለም፣ መንግስት ህዝቡን በሚያሸብርበት አገር ምን ህግ ሊኖር።በቃ ምን አለፋችሁ፣ በአሁኑ ሰአት ኢትዮጵያ ምድር አማራ መሆን ተኩላ ዋሻ ውስጥ የገባች በግ በሉት።

መንግስት በግልፅ የአማራን ዘር ለማጥፋት የማያቁዋርጥ ሽብር ላይ ነው። የመንግስት ወታደሮች በየሰፈሩ እየገቡ ወጣቱን እንደፈለጉ ያስራሉ፣ ገንዘብ ይቀበላሉ። ፋኖ ናችሁ ብለው ይረሽናሉ፣  ህግ ማን ያስከብር።

ኢትዮጵያ፣ ለአማራ የምድር ሲኦል ናት!!!


Comments

Popular posts from this blog

History of Debre Markos City