አማራ ከምድር እንዲጠፋ የተወሰነበት ነገድ!

በአሁኑ ጊዜ በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍና ጭፍጨፋ በቃላት ለመግለጥ አልችልም። በየደቂቃው ለሕይወቴ እፈራለሁ። የመንግስት ታጣቂዎች በሰፈራችን እየዞሩ ወንድ ልጆችን ፋኖ ናችሁ ብለው የገደሏቸውን ልጆች ሳስብ ከቤቴ በር ለመውጣት እፈራለሁ።  አማራ በመሆኔ ብቻ በማንኛውም ደቂቃ የአብይ አህመድ መልአከ ሞት መልክተኞች ከቤቴ አውጥተው ሊገድሉኝ ይችላሉ ብየ እፈራለሁ።  አክራሪ ናዚዎች  በከተማችን በየደቂቃው የሚበላውን የአማራ ነፍስ እያሰሰ እንዴት አድርገን ሰርተን እንብላ? አሁን ይሄን ብሎግ ስለጥፍ ራሱ በከተማችን ደብረ ማርቆስ ሃይለኞ የሆነ የጦርነት ድምጽ ይሰማኛል። 

የጥይት ተኩስ ያልሰማሁባቸውን ቀናት አላስታውስም፣ እያንዳንዷ የጥይት ጩኸት ደግሞ የንጹሃን ሰዎች አካል ላይ ያረፈች መሆንዋን ሳስብ ደግሞ ተስፋ የመቁረጥ፣ የማዘን፣ የመናደድ፣ ብቻ ሁሉንም ስሜቶች በአንዲት ቅጽበት አስተናግዳለሁ።  ለመኖር ያለኝ ጉጉት በእጅጉ ቀዝቅዟል።

እኔ ነገ አስፋልት ላይ እንደተገደለው እንደሌክቸረር ልማቱ ላለመሆኔ ምን ዋስትና አለኝ? በደምበጫና በዋድ ኢየሱስ ከየቤታቸው አውጥተው እንደገደሏቸው ልጆች ላለመሆኔስ? እያንዳንዷን ደቂቃ ከገዳይ መንግስት ለመደበቅ መሞከር እስከመቼ?  ይህን ሁሉ ግፍ አምኖ መቀበል የአማራነቴ ውርስ መሆኑ ነው?

አማራ ከምድር እንዲጠፋ የተወሰነበት ነገድ! ፍትህ  ግን ወዴት አለች?

እግዚአብሄር  ሆይ ፍረድ!

Comments

Popular posts from this blog

አማራ ላይ ግልፅ የዘር ማጥፋት

History of Debre Markos City